መስከረም 2012 ዓ.ም፡፡ ጂንካ ዩኒቨርስቲ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በጂንካ ዩኒቨርስቲ የአፈር ማረጋጊያ የረዥም ጊዜ የሙከራ ተግባር መፈጸሚያ የላብራቶሪ ምርምር ጣቢያ ተቋቁሟል፡፡ በዚህ የምርምር ጣቢያ ግንባታ ለእኛ ድጋፍ ላደረጉልን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን!
MNGD: news
ሁለት ጃፓናውያን ፕሮፌሰሮች በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ለተማሪዎች እና ተመራመሪዎች መስከረም 14 ቀን 2012 ዓ.ም ስለጂኦቴክኒካል ኢንጂነሪንግ ትምህርታዊ ገለጻዎችን ሰጥተው ነበር፡፡ከሁለት ሰአታት ትምህርታዊ ገለጻ በኋላ በትምህርታዊ ገለጻዎቹ ላይ ግልጽ የሆኑ ውይይቶችን አድርገው ነበር፡፡ከኪዮቶ ዩኒቨርስቲ ሚስተር ማትሱኩማ ሹንስኬ በፕሮጀክት አጠቃላይ/አጭር መግለጫ ወይም ግምገማ ላይ ገለጻ አድርጎ ነበር፡፡ ከኪዮቶ ዩኒቨርስቲ […]
በጂኦ ቴክኒካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያው ለህዝብ የተደረገ ገለጻ መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ባለ ቀዩ ምንጣፍ አዳራሽ ተካሄዶ ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ ለህዝብ ገለፃ ያደረጉት ዶ/ር ኢዋኢ (በናጎያ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ረዳት ፕሮፌሰር) እና ዶ/ር ሚያዛኪ (በኪዮቶ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር) የመንገድ ፕሮጀክታችን አባላት ናቸው፡፡ የዶ/ር ኢዋኢ ትምህርታዊ […]
ጃፓናዋያን ተመራማሪዎችና የሁለተኛ ዲግሪ ወይም የማስተርስ ኮርስ የሚከታተሉ ተማሪዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የመስፋፋት ችግር ያለበት የጥቁር አፈር (መረሬ) ፊዚካላዊ ባህሪያትን ላይ ምርምር ጀምረዋል፡፡
የመስፋፋት ችግር ያለበት ጥቁር አፈር (መረሬ) ምክንያት የሚደርሰውን የመንገድ አደጋ ለመቀነስ ከዕጽዋት ከሚገኙ የአፈር መጨመሪያ ንጥረ ነገሮች ማበልጸግና ማከናወን ፕሮጀክት የመጀመሪያ በጋር የተዋቀረው ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡ መርሀ ግብር፡ በ04/02/2012 (3፡30 እስከ 9፡30) ቦታ፡ ሳፋየር ሆቴል፣ አዲስ አበባ
በ17/08/2011 ጃፓናውያንና ኢትዮጵያውያን የምርምር ቡድን የመንገድ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ ወርክ ሾፕ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ አካሄዶል፡፡ በኢትዮጵያ ብዛት ያላቸው የገጠሩ ህብረተሰብ መንገዶች በደካማ አያያዝ ምክንያት የማይደረሱ ሆነው ቀርተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ገበያ፣ የጤና እና የትምህርት ተደራሽነት በእጅጉ ተስተጓጉሏል፡፡ ከአካባቢ ዕጽዋት አፈርን የሚያረጋጋ ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች በማልማት ፕሮጀክቱ የገጠር መንገድ ግንባታና ጥገና ሞዴል ለማልማት […]
በጋራ የተዋቀረ ኮሚቴ (ጄሲሲ) የመጀመሪያው ስብሰባ የተዘጋጀው በኦክቶበር 04/02/2012 በአዲስ አበባ ነው፡፡ በመጀመሪያ በጋር የተዋቀረው ኮሚቴ ችግር ባለባቸው አፈር ላይ የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ከዕጽዋት የተገኙ አፈር ጭማሪ ማበልጸግና ማከናወን ፕሮጀክት የመጀመሪያ ስብሳባ በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡ መርሀ ግብር፡ በ17/08/2011 (3፡30 እስከ 7፡00) PDF >>
ፕሮፌሰር ዮሺኖሪ ፉኩባያሺ አፈር ላይ የሚጨመር የማረጋጊያ ዘዴ፣ ሴልድሮል አሳይቶል፡፡ የፕሮጀክቱ አቻ የJICA እና JST ሰራተኞችንና የኢትዮጵያ አቻ ጨምሮ የመንገድ ፕሮጀክት ስለአቀደው ከአካባቢው ከሚገኙ ዕጽዋት ስለሚመረቱ የአፈር ጭማሪዎች ላይ ጥልቀት እውቀት እንዲኖራቸዉ አድርገዋል፡፡ ሴሊሎስ መሰረት ያደረገ አፈር ጭማሪ፡፡ ሴሌድሮል ውሃን በመምጠጥ የሚስፋፋ አፈርን ያረጋጋል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክት አባላት በመስከረም 2012 በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ጎብኝተዋል፡፡ የቡድን አባላቱ የመስፋፋት ችግር ያለበት ጥቁር አፈር (መረሬ) ስርጭት መርምሯል እናም ሴሉሎስ መሰረት ያደረገ አፈር ጭማሪ ግብዓት ለማምረት በአካባቢ ሊኖሩ የሚችሉ ዕጽዋት የመጀመሪያ ልየታ አድርጓል፡፡ የቡድን አባላቱ የአካባቢ ማህበረሰብ ለመንገድ ያላቸውን ፍላጎትንም አጥንቶል፡፡
በሴምተበር 26/01/2011 በተደረገው የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላት ሰብሰባ ቃለ ጉባኤው ተፈርሟል፡፡ የመንገድ ፕሮጀክት በጋር የተመሰረተው በJICA እና JST ሲሆን ይህም የጃፓን የልማት ድጋፍ (ኦዲኤ) እና ተወዳዳሪ የምርምር ፈንደ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ፕሮጀክት ድጋፍ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በኩል የፕሮጀክቱ አቻ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አና ጂንካ ዮንቨርሲቲ ናቸው፡፡ የጃፓን አቻ […]
ፕሮፌሰር ማኮቶ ኪሙራ እና ፕሮፌሰር ዮሺኖሪ ፉኩባያሺ የመንገድ ፕሮጀክት ቡድን የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ሲቪል ኢንጅነሪንግ ትምህርት ቤት ላብራቶሪን ጉብኝተዋል፡፡ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ሲቪል ኢንጅነሪንግ ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ የፕሮጀክት አስተናጋጅና ተግባሪ የኤጀንሲ ነው፡፡ በተጨማሪም ለፕሮጀክቱ የቢሮ ቦታን ያመቻቻል፡፡ በርከት ያሉ የኢኒስቲትዩቱ ተመራማሪዎችም በትግበራው ላይ ለመሳተፍ አቅደዋል።