የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የመንገድ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ ወርክ ሾፕ በአዲስ አበባ

በ17/08/2011 ጃፓናውያንና ኢትዮጵያውያን የምርምር ቡድን የመንገድ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ ወርክ ሾፕ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ አካሄዶል፡፡
በኢትዮጵያ ብዛት ያላቸው የገጠሩ ህብረተሰብ መንገዶች በደካማ አያያዝ ምክንያት የማይደረሱ ሆነው ቀርተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ገበያ፣ የጤና እና የትምህርት ተደራሽነት በእጅጉ ተስተጓጉሏል፡፡ ከአካባቢ ዕጽዋት አፈርን የሚያረጋጋ ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች በማልማት ፕሮጀክቱ የገጠር መንገድ ግንባታና ጥገና ሞዴል ለማልማት በማሰብ የመስፋፋት ችግር ያለበት ጥቁር አፈር (መረሬ) ለመቅረፍ አልሟል፡፡ በጃፓን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ (ጄሲቲ) እና የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጂአይሲኤ)፣ የኪዮቶ ዪንቨርሲቲ በጃፓን አጥኒዎች የተመሰረተው ዓለም አቀፋዊ የጋራ የጥናት ቡድን፣ የሚያዛኪ ዩንቨርሲቲ፣ ኢሂሜ ዩንቨርሲቲ፣ ናጎኛ የቴክኖሎጂ ኢኒስትቲዩት፣በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎችና ተግባሪዎች፣ ጅንካ ዩንቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የተመሰረተ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በሚያዝያ 2012 የሚጀመር ሲሆን ለሚቀጥለው 5 ዓመታት ይቀጥላል፡፡
የወርክ ሾፑ መጀመሪያ የተሰናዳው በፕሮፌሰር ማኮቶ ኪሙራ (የማዕንዲስና ድህረ ምረቃ ትምህርት፣ ኪዮቶ ዩንቨርሲቲ) እና ፕሮፌሰር ማሳዮሽ ሺጌታ(በኪዮቶ ዩንቨርሲቲ የአፍሪካ አካባቢ የጥናት ማዕከል ዳይሬክተር) ነው፡፡ የኢትዮጵያ ተመራማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በወርክ ሾፑ ተካፍለዋል፡፡
በወርክ ሾፑ መጀመሪያ ላይ፣ ፕሮፌሰር ኑርልኝ ተፈራ (የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት) እና ፕሮፌሰር ገብሬ ይንቲሶ ዴኮ (የጂንካ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት) ሁለቱም ዩንቨርሲቲዎች በ2007 መጨረሻ ላይ የተመሰረቱ አዲስ የምርምር ኢንስትትዩት እንደመሆናቸው መጠን በጋር በአለም አቀፍ ጥናት አማካኝነት የጥናት አቅም እንደሚያጎለብትና የሰው ሀይል እንደሚያለማ ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡ ፕሮፌሰር ማኮታ ኪሙራ በ እንግሊዘኛ ምፃረ ቃል “መንገድ” የሚለው የፕሮጀክቱ ስም መንገድ ከሚለው የአማርኛ ቃል የተመሳሰለ ሲሆን አለም አቀፍ የጋራ ጥናት ለሁለትዮሽ የ ምርምር ትብብር አዲሰ መንገድ እንደሚከፍት አጽኖት ሰጥተዋል፡፡
የተከበሩ አምባሳደር ዳይሱኬ ማትሱናጋ የጥናቱ ውጤት ለኢትዮጵያ ማህበረሰብ አስተዋጾኦ እንደሚያበረክት እንዲሚጠብቁ ገልጸዋል፡፡