የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

1ኛው አአሳቴዩ ለህዝብ የተደረጉ ትምህርታዊ ገለጻ

በጂኦ ቴክኒካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያው ለህዝብ የተደረገ ገለጻ መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ባለ ቀዩ ምንጣፍ አዳራሽ ተካሄዶ ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ ለህዝብ ገለፃ ያደረጉት ዶ/ር ኢዋኢ (በናጎያ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ረዳት ፕሮፌሰር) እና ዶ/ር ሚያዛኪ (በኪዮቶ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር) የመንገድ ፕሮጀክታችን አባላት ናቸው፡፡

የዶ/ር ኢዋኢ ትምህርታዊ ገለጻ ርእስ “አድቫንስድ ቴክኒክ ኦፍ ትሪያዣል ኮምፕሬሽን ቴስት፡ የጋዝ – ሃይድሬት –  ተሸካሚ የአፈር አይነቶች” ሲሆን፥ በጃፓናያውያኑ የደሴት ስብስቦች / ኣርችሂፐላጎ/  በሚገኙ የባህር ወለል ሜቴል ሃይድሬት ከመጠን በላይ በብዛት እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የሚቴን ጋስ በማምረት ሂደት የሚቴን ሃይድሬት የያዘው የባህር ወለል በተከታታይ ይቆፈራል፡፡ ስለዚህ በጥንቃቄ እና ውጤታማ/ቅልጥፍና ባለው መልኩ የሚቴን ሃይድሬትን ለመሰብሰብ የሚቴን ሃይድሬት የያዙትን ሰድሜንቴሽን/የደለል ዝቃጭ ቅሪት አካል ሜካኒካዊ ባህሪያት መግለጽ ጠቃሚ ነው፡፡ በዚህ ትምህርታዊ ገለጻ ውስጥ የ“አድቫንስድ ትሪያግዣል ኮምፕሬሽን ቴስት” (የላቀ የባለ ሶስትዮሽ ጎን ጫናን የመቋቋም የሙከራ ተግባር) እና የሙቀት መጠናቸው በቀላሉ ሊለዋወጥ የሚችሉና የአየር ግፊት ሁኔታዎችም ሲለዋወጥ በቀላሉ ሊቋቋሙ የሚችሉ የመሳርያ አይነቶች በተሰጠው ትምህርታዊ  እንዲተዋወቅ ተድርጓል፡፡  የሙከራ ተግባሩ ስነ ስርአቶች የሚቴን ሃይድሬት ይዘት ያላቸውን የአፈር ቅንጣት ናሙናዎችን የመፍጠርና ተከታታይ የባለ ሶስትዮሽ ጎን ጫናን የመቋቋም የሙከራ ተግባር/ሲሪየስ ኦፍ ትሪግዣል ኮምፕሬሽን ቴስትስ) እንዲተዋወቁም  ተድርጓል፡፡

የዶ/ር ሚያዛኪ ትምህርታዊ ገለጻ ዋናው ርእስ “ከአካላዊ ሞዴሊንግ እና የቁጥር ማስመሰል ጋር የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት  አቀራረብ ዘዴ (An approach to seismic damage mechanism with physical modeling and numerical simulation) የሚል ነበር፡፡ በአለም ላይ ካሉት ሌሎች አካባቢዎች ይልቅ በጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ በይበልጥ በተደጋጋሚ ስለሚከሰት የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያደርሳቸው ጥፋቶች በጃፓን እጅግ አስፈላጊው እና አስገዳጅ የምርምር ርእሰ ጉዳይ ነው፡፡ የትምህርታዊ ገለጻው አላማ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በትክክለኛው የመሬት አቀማመጥ/መዋቅሮች ላይ በስፋት እንዴት በችግሩ የደረሰውን ጉዳት ልናይ እንደምንችልና ከመሬት መንቀጥቀጥ ሲሙሌሽን/በላብራቶሪ ትክክለኛውን ድርጊት የማየት ጉዳይ እንዴት እንደሆነ የሚያተኩር ነበር፡፡ በዚህ ትምህርታዊ ገለጻ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ወቅት የምርምሮቹን ሞዴል በመጠቀም እና የአቅጣጫ ማስቀየሪያ መዋቅሮችን በቁጥር ትንተና በመስጠት በመንገድ ጠርዞች የተፈጠሩ ጉድጓዶችን መልሶ የመሙላት ተግባራትን ለመዘርጋት የጉዳት ሜካኒዝሙን ለማብራራት እንደምሳሌዎች የተጠቀመበትን ዘዴዎች ተናግሮ ነበር፡፡ በዚህ የጥያቄ እና መልስ ትምህርታዊ ገለጻ ክፍለ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ከትሪያግዣል ኮምፕሬሽን ቴስት /ባለሶስትዮሽ ጎን ጫናን የመቋቋም የሙከራ /ተግባር እና የመሬት መንቀጥቀጥ ምልከታዎችን ምሳሌዎች ጋር የተገናኙ  የመሳርያ አይነቶች ጉዳይ ተነጋግረዋል፡፡  የውይይት ጊዜው እያንዳንዳቸው በሌሎች ምርምሮች የጋለ ስሜት

እንዲሰማቸው ለማድረግ ነው፡፡