ርእሰ ጉዳዮች አና ችግሮች
የመንገድ መሰረተ ልማት ልማት ለአንድ ሀገር ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ልማት ውሳኝ ነው ። የመስፋፋት ባህሪ ያለው የጥቁር አፈር (መረሬ) በኢትዮጵያ ከ 10 በመቶ የሚበልጠውን የመሬት አካል የሚሸፍን ሲሆን፣ በመንገድ መሰረት ልማት አደጋ በማስከተል ትልቅ አንቅፋት ሆኖ ቆይቷል ። ጥቁር አፈር (መረሬ) በውሃ መጠን ይዘቱ ስለሚለዋወጥ ፣ ከእርጥበት መጨመር በሚፈጠር የእብጠት ግፊት የመንገዱን አወቃቀር ከፍ ያደርገዋል ፣ በተቃራኒው የመጭማደድ ግፊት ደግሞ አቀማመጡ ልዩነት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡
በተለምዶ ውድ ዋጋ የሚያስከፍሉ እርምጃዎች ችግሩን ለመፍታት የተሞከረ ሲሆን፣ ይህም የመስፋፋት ባህሪ ያለው የጥቁር አፈር (መረሬ) በየተሻለ ጥራት ያለው የመተካት የመሳሰሉት ተሰርተዋል፡፡ ጥራት ያለው አፈር እጥረት ለመቀነስና ከፍተኛ የማጓጓዥ ወጪያቸውን ለመቋቋም የአፈር ጭማሪዎቸ የአፈር ጥራትን ለማሻሻል የሚረዱ አማራጭ ዘዴ ተደርገው ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጂ በውጤታማነታቸው ላይ ያተኮረ ጥናትና ምርምር ውስን በመሆኑ የአፈር ጭማሪ በውጤታማነት ተቀባይነት አላገኙም፡፡
የፕሮጀክቱ ዓላማ
የዚህ ፕሮጀክት ዓላማ ጥርጊያ ያልተከናወነባቸውን መንገዶችን ከፍተኛ ጉልበትን በሚጠይቁ ቴክኖሎጂና በአካባቢው በሚገኝ ግብአቶች የሚጠገንበትን ስርዓት ለማዘጋጀት ነው፡፡ ስርዓቱ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የመስፋፋት ባህሪ ያለው የጥቁር አፈር (መረሬ) ያለባቸውን ቦታዎች በመንገድ ላይ የሚያስከትለው ውድመቶችን ለመቀነስ ውጤታማ ነው፡፡
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ግብ ሁሉን ቀበሌዎች ባቅራቢያ ካሉት በጋ ከ ክረምት መንገዶች ጋር ለማገናኘት አስተዋጾኦ ለማድረግ ነው፡፡ እንዲሁም በአካባቢው ባለ የሀብት ምንጭ የሚጠቀም ፈጠራ የታከለበት አፈርን የማጠናከር ቴክኖሌጂ በመጠቀም የገጠር ማህበረሰብን ፍላጎት ለሟሟላት አስተዋፆኦ ያደርጋል፡፡
ይህንን አጠቃላይ ግብ ለማሳካት ፕሮጀክቱ ከእፅዋት የሚገኙ የአፈርን የሚያክሙ ጭማሪዎችን ለማዘጋጀት ቴክኖሌጂውን በሀገር አቀፍና በአካባቢያዊ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ በውጤታማነት ስራ ላይ ለማዋል ደረጃ ያስቀምጣል፡፡
በተጨማሪም የአካባቢ የሀብት ምንጭ ላይ መሰረት ያደረጉ ዘዴዎችን በመውሰድ ማለትም በአካባቢ የሚገኙ ግብአቶችንና ሙያ የሌላቸውን የሰው ሀይል በውጤታማነት በመጠቀም ፕሮጀክቱ የገጠርን የስራ ዕድል ለሴቶችና ለወጣቶች በገጠር መንገድ ግንባታና ጥገና ኔትወርክ ውስጥ በመቅጠር የገጠርን የስራ ዕድልን በመፍጠር የገጠርን ተደራሽነትን ለማሻሻል ያለመ ነው፡፡