የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

2ኛው በአአሳቴዩ ለህዝብ የተደረጉ ትምህርታዊ ገለጻዎች

 ሁለት ጃፓናውያን ፕሮፌሰሮች በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ለተማሪዎች እና ተመራመሪዎች መስከረም 14 ቀን 2012 ዓ.ም  ስለጂኦቴክኒካል ኢንጂነሪንግ ትምህርታዊ ገለጻዎችን ሰጥተው ነበር፡፡ከሁለት ሰአታት ትምህርታዊ ገለጻ በኋላ በትምህርታዊ ገለጻዎቹ ላይ ግልጽ የሆኑ ውይይቶችን አድርገው ነበር፡፡ከኪዮቶ ዩኒቨርስቲ ሚስተር ማትሱኩማ ሹንስኬ በፕሮጀክት አጠቃላይ/አጭር መግለጫ ወይም ግምገማ ላይ ገለጻ አድርጎ ነበር፡፡

 ከኪዮቶ ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ሰዋሙራ ያሱኖ ፋይን ሽሬድድ ፔፐር በመጠቀም በከፍተኛ ጭቃ የተዋጠ ውሃን ማከም የሚቻልባቸውን ቴክኒኮች በትምህርታዊ ገለጻ ተናግረው ነበር፡፡

ከናጎያ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የመጡት ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ሂሮማሳ ኢዋኢ በስሱ የተቆራረጠ ወረቀት ስራዎችን በሰርቶ ማሳያ ምን እንደሚመስል አሳይቷል፡፡ ከኢሂሚ ዩኒቨርስቲ የመጡት ፕሮፌሰር፣ ዶ/ር ሂዲኪ ያሱሃራ የባዮካታሊስት በመጠቀም ስለ ባዩሲሜንቲንግ ቴክኒክ ተናግረው ነበር፡፡ በመሬት መንቀጥቀጥ የሚነሱ የከርሰ ምድር ውሃ ሊኪፋክሽን በመቀነስ የአፈር ሁኔታን ለማሻሻል ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን ቴክኒኮች አሳይቷል፡፡ ከገለጻው በኋላ ከተሳታፊዎቹ በቀረቡት አብዛኛዎቹ ጥያቄዎች ላይ ውይይቶች በንቃት ተካሄደው ነበር፡፡