የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

ማህብረሰቡን ያሳተፈ የመንገድ ጥገና ስራ በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ

በታህሳስ 2019 በፕሮጀክቱ በተሰራ መንገድ ላይ ያጋጠመን የመንገድ ብልሸት እ.ኤ.አ. በህዳር 2022  የአካባቢው ሰዎችን በማሰተፍ መጠነኛ ጥገና በማድረግ የመንገድ ማሻሻያ ስራ ተካሂዷል፡፡

በዚህ የፕሮጀክት ሂደት  የምርምር ቡድኑ የሚገጥሟቸውን የተለያዩ ሁኔታዎችን እያስታዋሉና እየተመረመሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም አሳታፊ የግንባታ ዘዴዎችን ለማፈላለግ ተጠቅመውበታል። ከዚህ በተጨማሪ ይህ የመንገድ ጥገና ማሳያ መንግስት፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና አካባቢው ማህበረሰብ በመተባበር  ዘላቂ እና የተደራጀ የመንገድ ጥገና ዘዴን ለመዘርጋት እንደ ማሳያ ሆኖ ያገለግላል። በቀጣይም በፕሮጀክቱ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ውጤታማ የሆኑ የመንገድ ልማት ዘዴዎችን በመዳሰስ ስራውን ይቀጥላል፡፡