የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

4ኛው የMNGD ዓለም አቀፍ የተማሪዎች አውደ ጥናት

4ኛው የMNGD አለም አቀፍ የተማሪዎች አውደ ጥናት በጥር 30፤ 2023 (16፡00JST~/10፡00 EAT) በበየነመረብ ተካሄዷል። በመጀመሪያ በሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ተማሪ የሆኑት አቶ አለምሸት በቀለ ታደሰ “An experimental study on the coupled effect of diatomaceous earth and hydrated lime in expansive soil” በሚል ርዕስ የምርምር ውጤታቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ በመቀጠልም በኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ተማሪ የሆኑት አቶ ተሾመ ብርሃኑ ከበደ “Permeability of Soils Treated with Fine Shredded Paper (FSP)”  በሚል ርዕስ የምርምር ስራቸውንአቅርበዋል። በዚህ አውደ ጥናት አቶ ፍሬሃይለአብ አድማሱ ጊዴቦ በሁኔታዎች አለመመቸት ምክንያት አልተገኙም።

በአውደ-ጥናቱ ከጃፓን አባላት በተጨማሪ የአ.አ.ሳ.ቴ.ዩ እና ERA አባላት በውይይቱ ተሳትፈዋል።