የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

4ኛው የጋራ አስተባባሪ ኮሚቴ (JCC) በአዲስ አበባ  ስብሰባ ተካሂዷል

4ኛው የጋራ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ እ.አ.አ.መስከረም 1 ቀን 2022 በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ይህ ስብሰባ  እ.አ.አ ከ2019 ወዲህ የመጀመሪያው የፊት ለፊት ስብሰባ ሲሆን በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ አመት የተካሄደ የመጀመሪያው የጋራ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባም/JCC/ ነበር። በስብሰባው ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ መምጣት ያልቻሉ የጃፓን ተሳተፊዎችን እንዲሁም የኢትዮጵያ አቻዎቻችው በስብሰባው እንዲሳታፉ   የበየነመረብ ቴክኖሎጂን /zoom meeting/  ተጠቅመናል። ከጃፓን እና ከኢትዮጵያ የተወጣጡ በአጠቃላይ 22 ሰዎች በቦታው በአካል የተገኙ ሲሆን 15 ሰዎች ደግሞ በበየነመረብ/ Zoom/ስብሰባውን ተሳትፈዋል። በስብሰባው ላይ ከኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ፣ ከሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኢሂሜ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ እና ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ከተውጣጡ የፕሮጀክት አባላት በተጨማሪ ከጃይካ ኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት እና ከጄኤስቲ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ ዶ/ር አብርሃም (የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት)፣ ወይዘሮ ሂሮሴ (የጃይካ ኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ምክትል ዋና ተወካይ) እና የፕሮጀክቱ መሪ ፕሮፌሰር ኪሙራ (የኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ) ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ከረዥም ጊዜ ቆይታ በኋላ ፊት ለፊትለመገናኘት መቻሉ ትልቅ ደስታን እንደፈጠረባቸው አንስተወ፤የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በፈጠረው  ተፅዕኖ ሳቢያ ነገሮች በሚጠበቀው ልክ እየሄዱ ባልነበሩበት ወቅት እንኳን የፕሮጀክቱ ስራ እንዳይቋረጥ  በየነመረብን እና መሰል ቴክኖሎጂን በመጠቀም  ሲሰሩ የቆዩትን የጃፓን እና የኢትዮጵያ ተመራማሪዎችን ጥረት አድንቀው እውቅና ሰጥተዋል።በንግግራቸውም የፕሮጀክቱ ስራ በተቋሞች መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ የሚያጠነክር በመሆኑ ፕሮጀክቱን ይበልጥ ለማስተዋወቅ ያላቸውን ፍላጎት አረጋግጠዋል።

በስብሰባው የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ የጃፓን እና የኢትዮጵያ ተመራማሪዎች ፕሮጀክቱ ባለፉት ሶስት ዓመታት ተኩል ውስጥ ያለፈበትን እያንዳንዱን ሂደት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል። በጥያቄ እና መልስ ክፍለጊዜም ዝርዝር ነገሮች ተነስተው የፕሮጀክቱ ወቅታዊ ሁኔታ እና የወደፊት እቅዶች በተመለከተ በተሳታፊዎች ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።

የስብሰባው የሁለተኛ አጋማሽ ለተሳታፊዎች ለውይይት በቂ ጊዜ የሰጠ ነበር። በውይይቱ ወቅትም በቀረው ጊዜ ለፕሮጀክቱ እንዴት አስተዋፅዖ ማበርከት እንችላለን? ምን ውጤት ማምጣት እንችላለን? እና እንዴት ነው በጋራ መስራት ያለብን? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ሁሉም ተሳታፊ ትብብሩን የተሸለ ደረጃ ላይ ያደርሰል ያለውን ሃሳብና አስያየታቸውን በነፃነት እና በንቃት ሰንዝረዋል።

በዚህ ጊዜ የተገነዘብነው ነገር ቢኖር ፊት ለፊት መወያየት ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን ነበር። ሆኖም፣ ይህ ሊሆን የሚችለው ከኮቪድ-19 አደጋ ስንላቀቅ በመሆኑ እከዝያ ጊዜ በተለመደው የበየነመረብ ላይ ውይይቶች መቀጠል ተገቢ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጠናል። ሆኖም ፊት ለፊት የተደረገው ውይይት ለጃፓንም ሆነ ለኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ሀሳብ የመለዋወጥ እድል የሰጠ ስለነበረ ፕሮጀክቱን በኢትዮጵያ የበለጠ ለማስተዋወቅ እጅግ ጠቃሚ ነበር።