የአጭር ጊዜ ስልጠና ተሳታፊዎች ቡድኑ በቀጣይ በኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ምረቃ ትምህርት ቤት ወደሚገኝበት ወደ ካትሱራ ካምፓስ ሄደው በፕሮፌሰር ኪሺዳ በተሰጠው የጋራ ሴሚናር ላይ ለመሳተፍ ችለዋል።
![](https://mngd.africa.kyoto-u.ac.jp/mngd/wp-content/uploads/2022/12/IMG_2984-1024x695.jpg)
አቶ በላቸው፣ አቶ ይታየው እና አቶ አየነው ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ስራዎቻቸውን/ፕሮጀክቶቻቸውን/ አቅርበዋል። ይህም ለተማሪዎቹ በተለያየ መንገድ የምርምር ፕሮጄክቶች እና ጥናቶቻቸውን የሚያቀርቡበት ትልቅ እድል የሰጠቸው ነበር። በቦታው ላይ ከMNGD ፕሮጀክት ፕሮፌሰር ያሱሃራ (ኤሂሜ ዩኒቨርሲቲ) ጋርም የመነጋገር እድል ነበራቸው።
![](https://mngd.africa.kyoto-u.ac.jp/mngd/wp-content/uploads/2022/12/IMG_2999-1024x760.jpg)