የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የማህበረሰብ አቀፍ የትምህርት ማዕከልን ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ የማስረገብ ር ስነ-ስርዓት ተካሄደ

እ.ኤ.አ ጥቅምት 26 ቀን 2022 ከሰአት በኋላ  በጃፓን ኤምባሲ Grassroots Human Security ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ የጃንካ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባውን የሁለገብ አዳራሽ (የማህበረሰብ የመማሪያ ማዕከል/ CLC) የማስመረቅና ለዩኒቨርሲቲው የማስረከብ ስነ-ስርዓት ተከናውኗል። በርክብክቡ ስነ-ስርዓት ላይ በኢትዮጵያ ከጃፓን ኤምባሲ እና ከጃይካ ኢትዮጵያ ቢሮ ከተውጣጡ ስድስት ሰዎች በተጨማሪ የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ተወካዮች የኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ ሶስት አባላትና የመንገድ አስተዳደር እና ሌሎችም በደቡብ ኦሞ ዞን የMNGD ፕሮጀክት ተግባር ላይ የተሰማሩ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ሪባን የመቁረጥ ሥነ-ሥርዓት ከግራ ወደ ቀኝ፣ ዶ/ር ኩሴ (የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት)፣ ታደሰ ካይ (የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ)፣ ሚስተር ታካሺ (የጃፓን ተጠባባቂ አምባሳደር፣ የኢኮኖሚ ትብብር ዳይሬክተር) ፎቶ በ አያካ ታናካ

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት የነበሩት ፕሮፌሰር ገብሬ ይንቲሶ ይህንን የምርምርና የማህብረሰብ አገልግሎት መዕከል ግንባታ ሃሳብ ከMNGD ፕሮጀክት ጋር መተባበር ሲጀምሩ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ለጃፓን ኤምባሲ ጥያቄ አቅርበው ኤምባሲውም ጥያቄውን ተቀብሎ ድጋፍ እንደደረገ ለማወቅ ተችሏል። ምንም እንኳን ግንባታው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ የዘገየ ቢሆንም፣ የMNGD ፕሮጀክት አባል የሆኑት ዶ/ር ፉኩባያሺ (የሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ) በህዳር ወር ጂንካ ሲጎበኙ ቀጣይ አስተዳደር ስልጠናን በዚህ መዕከል /በCLC/  ዕቅድ/ምኞት የነበራቸው ሲሆን፤ ሃሰባቸው ግቡን መቶ መገኘቱ ደግሞ  የጃፓን ዕርዳታ ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ መደረጉን በተግበር ያሰየ ጥሩ ምሳሌ እንደሆነ በርክብክቡ የተሳተፉት ሰዎች አዎንታዊ ምላሽ  መረጋገጨ ነበር።

ሁሉም ተሳታፊዎች በጃፓን ባንዲራ እና በጂንካ ዩኒቨርሲቲ አርማ ያጌጡ የመታሰቢያ ሸሚዞችን ለብሰዋል። ዶ/ር ኩሴ (የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት) የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና የትምህርት ፖሊሲ እና የወደፊት ራዕይን አስተዋውቀዋል, አዲስ የተጠናቀቀው CLC በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚኖረውን ሚና በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ፎቶ በሁሉም ተሳታፊዎች።