የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የአጭር ጊዜ ስልጠና፡ በኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ የሲቪል ምህንድስና ቤተ ሙከራ

እ.ኤ.አ. ታህሳስ 2 ቀን 2022 ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እና ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተውጣጣው የስልጠና ቡድን የሲቪል እና ምድር ሃብቶች ምህንድስና ትምህርት የሚገኝበትን ኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ ካትሱራ ካምፓስን ጎብኝቷል።

በጉኝታቸው ወቅትም የMNGD ፕሮጀክት አባል በሆኑት ስለኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ የሲቪል ምህንድስና አጭር መግለጫ ከተደረገ በኋላ ቡድኑ የንፋስ ዋሻ ክፍልን (መዋቅራዊ ምህንድስና ላብራቶሪን) ጎብኝቶ  በዶ/ር ኖጉቺ እየተመረ ወደ ሃይድሮሊክ ሜካኒክስ ክፍል አምርቷል። በሃይድሮሊክ ሜካኒክስ ቤተ-ሙከራም በዶ/ር ኦቶዳ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

የንፋስ መሿለኪያ ክፍል (ዶ/ር ኖጉቺ)
የሃይድሮሊክ ሜካኒክስ ክፍል (ዶ / ር ኦቶዳ)

ቡድኑ በመቀጠል የMNGD ፕሮጀክት ሙከራዎች የሚካሄዱበትን የጂኦቴክኒካል ኢንጂነሪንግ ላብራቶሪ ተጎብኝቷል፡፡በዶ/ር ኪዶ እና ከMNGD ፕሮጀክት አለም አቀፍ ተማሪዎች መካከል አንዱ በሆኑት በአቶ ተሾመ አማካይነት ቤተ ሙከራዎች ውስጥ ገለፃ እና ለተነሱትን ጥያቄዎቸ በቂ ምላሽ ተሰጥቷቸው  እጆቻቸው ማስታወሻ ለመያዝ እስክደክሙ ድረስ  ሲጽፉም ነበር፡፡.