ሳትረፕስ/መንገድ (SATREPS/MNGD) ፕሮጀክት ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን በዚህ ዓመት ከኢትዮጵያ በድጋሚ በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡ ለፕሮጀክቱ እንቅስቃሴ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ያሉ ሶስት መምህራን በአሁኑ ወቅት ወደ ጃፓን መጥተዋል፡፡ አንዱ መምህር ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ሲሆን ሁለቱ መምህራን ደግሞ ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ናቸዉ፡፡
በሚያዝያ ወር አቶ ተሾመ ብርሃኑ ወደ ኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ድህረ ምርቃ ትምህርት ቤትን እንዲሁም አቶ ካሳሁን የማነ እና አቶ አርጋቸዉ ቦቸና ወደ ኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ የእስያና የአፍሪካ አካባቢ ጥናት ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤትን ተቀላቅለዋል።
ምንም እንኳን በCOVID-19 ስርጭት ምክንያት ጃፓን የምመጡበት ጊዜ ቢዘገይም ሶስቱም በሰኔ ወር ጃፓን የደረሱ ሲሆን የበሽታዉን ስርጭት ለመከላከል ሲባል ለሁለት ሳምንታት በማቆያ ዉስጥ ከቆዩ በኃላ ወደሚማሩብርት ዩኒቨርሲቲዎች ገብተዋል።ይህም በአሁኑ ጊዜ በጃፓን ዩኒቨርሲቲዎች የሚያጠኑ የመንገድ (MNGD) ፕሮጀክት ተማሪዎች ጠቅላላ ቁጥርን አቶ አለምሸት ከሚያዛኪ (Miyazaki) ዩኒቨርሲቲ እና አቶ ፍሬሃይሌአብ ከኢህሜ (Ehime) ዩኒቨርሲቲ ጨምሮ ወደ አምስት አድርሶታል።