21ኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ጥናት ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2022 ተካሂዷል። የSATREPS-MNGD ፕሮጀክት አባል ፕሮፌሰር ሺጌታ በ29ኛው ቀን የፓናል ዝግጅት አዘጋጅተው የነበረ ሲሆን በፓናል ዝግጅቱ ሚስተር ማትሱኩማ እና ዶ/ር ካኔኮ የ SATREPS-MNGD የፕሮጀክት እንቅስቃሴዎች እና የተገኙ የምርምር ውጤቶችን .አቅርበዋል። ከፕሮጀክቱ አባላት፤ ከኢትዮጵያውያን ምሁራንና ከተመራቂ ተማሪዎች እንዲሁም ከፕሮጀክቱ ግንኙነት ከሌላቸው ተማሪዎች የተቀበልናቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች የፕሮጀክቱን አስፈላጊነትና ጥንካሬ ያረጋገጡ ነበሩ። በአለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ከተለያዩ ክልሎች ከተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች ጋር የመገናኘት እና የሐሳብ ልውውጥ የማድረግ ዕድሉ ፕሮጀክቱን ወደፊት ለማራመድ እጅግ ጠቃሚ መንገድ ነበር።