የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

ፕሮፌሰር ኪሙራ በአ. አ.ሳ. ቴ. ዩ. ያደረጉት ቁልፍ ንግግር / Keynote/

7ኛው ዓመታዊ የምርምር ኮንፈረንስ “ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ/ Innovation /ለኢንዱስትሪ” በሚል መሪ ሃሳብ ከግንቦት 4-5 ቀን 2023 በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል። የኮንፍራሱ ተጋባዥ የነበሩት የፕሮጀክታችን መስራችና  ዋና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ኪሙራ በኮንፈረንሱ ላይ “ለመዋቅሮች መሰረት የሚሆኑ አዲስ የቴክኖሎጂ አስተሳሰብ ከተለያየ አቅጣጫ ” በሚል ርዕስ ቁልፍ ንግግር// Keynote/ አቅርበዋል።  ፕሮፌሰሩ “ከተለየየ አቅጣጫ ማሰብ” በፈጠራ ውስጥ ምን የህል አስፈላጊ እንደሆነ በተጨባጭ ምሳሌዎች በማስደገፍ አብራርቷዋል፡፡ ከተጠቀሱት ምሳሌዎች መካካል ከታላቁ ሀንሺን የመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ በፍጥነት መንገዶች ላይ ለደረሱት በርካታ የኮንክሪት ቱቦዎች ውድመት ምላሽ ለመስጠት ምሰሶዎችን ከማቆም ይልቅ ማወዛወዝን የሚስብ የቴክኖሎጂ  የጃፓን  ኩባንያዎች ማስተዋወቃቸዉን አንስተዋል፡፡

ተማሪ በነበሩበት ጊዜ የሰሃራ በረሃ በብስክሌት ጉዞ ጀምረው ከ20 በላይ የአፍሪካ ሀገራትን የጎበኙት ፕሮፌሰር ኪሙራ አሁኑ የዶ-ኑ / Do-nou method /ዘዴን በመጠቀም የመንገድ ሁኔታን ለማሻሻል  በዓለም ዙሪያ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አስተዋውቀዋል። በመጨረሻም ፕሮፌሰሩ “እባካችሁ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ፣ ዝቅተኛ ቴክኖሎጂን እና መካከለኛ ቴክኖሎጅዎችን በማዋሃድ ጥሩ አገር ለማፍጠር ጥረት አድርጉ” ሲሉም ለኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል። ታዳሚዉን ፈገግ የሚያስብል  አልፎ አልፎ በተሰብሳቢው ላይ ሳቅን በሚፈጥር አቀራረብ ንግግር ያደረጉተ ፕሮፌሰር ኪሙራ በአ.አ.ሳ.ቴ.ዩ. ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም በመምህራንና አባላት እንዲሁም በተማሪዎች ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡