ጂንካ ዩኒቨርስቲ ከፕሮጀክቱ አስፈጻሚዎች አንዱ በመሆኑ በጋራ በመሆን ስለሚሰራው የምርምር ፕሮጀክት አስተዋውቆ ነበር፡፡የእድገት አጋሮች ጥምረት የጃፓን ኩባንያ ሲሆን ከጂንካ ዩኒቨርስቲ ጋር በገባው ስምምነት የጋራ የምርምር ፕሮጀክትን በማቋቋም ማጎልበት እና የመንገድ ፕሮጀክት የምርምር ተግባራትን በጥልቀት ለማስረጽ ነበር፡፡ የጋራ ምርምር ስራው በትምህርት/አካዳሚ/ኢንዱስትሪ/መንግስት የጋራ ትብብርን ለማስረጽ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት የሚጠበቅበት ሲሆን የመንገድ ፕሮጀክትን በስፋት ወደ ሌሎች አካባቢዎችም ለማስፋፋት ጥረት ያደርጋል፡፡