የሥልጠና ተሳታፊዎች ቡድን ከሚስተር ሃጊዋራ ጋር ሐሙስ ታኅሣሥ 8 ቀን ከኢታሚ አየር ማረፊያ ወደ ሚያዛኪ ሲመጡ በሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ የMNGD ፕሮጀክት አባል የሆኑት ዶ/ር ፉኩባያሺ፣ ፕሮፌሰር ካሜይ እና በዩኒቨርሲቲው የMNGD ፕሮጀክት አለም ዓቀፍ ተማሪ አቶ አለምሸት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በቀጣዩ ቀን አርብ ዕለት የጂንካ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች የሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የምህንድስና ፋኩልቲ ዲንን በአክብሮት ጉብኝተዋል፡፡ በመቀጠልም የሲቪል ምህንድስና ላቦራቶሪዎችን እና የመሳሪያ ትንተና ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡ በዚህ ወቅትም.በሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ የሆኑት አቶ አለምሸት በአፈር ላይ እየሰሩ ስላሉት ሙከራዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተጨማሪም የሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ ላቦራቶሪዎችን አመራር ስረዓትን በመጥቀስ በኢትዮጵያ የምርምር ተቋም ውስጥ ያሉትን ቤተ-ሙከራዎች እና የሙከራ አካባቢን የበለጠ ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
ቡድኑ ከሰአት በኋላ በሞገድ የተፈጠሩና የአፈር መሸርሸርን መቋቋም በሚችሉ የአሸዋማ ድንጋይ ንጣፎች እና ደካማ የድንጋይ ንጣፍ ቦታዎችን “Oni no Sentakuita” (Demon’s Washboard) ጎበኝተዋል። የቡድኑ አባላት በአኦሺማ ደሴት ላይ ቆመው ይህንን በተፈጥሮ የተፈጠረውን መልከዓ ምድር/ geological formation/ በአድናቆት ስመለከቱ ተስተውለዋል፡፡