የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

2ኛው የጋራ የማስተባበርያ ኮሚቴ ስብሰባ

ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም 2ኛው የጋራ ማስተባበሪያ ኮሚቴ ስብሰባ በኮቪድ-19 ተጽእኖ ምክንያት በጋራ ከመሰባሰብ ይልቅ ወይም በአካል ይልቅ በኢንተርኔት በተሳካ ሁኔታ ተካሂድዋል  ፡፡
ተሳታፊዎቹ የሚከተሉት ነበሩ፡
ከኪዮቶ ዩኒቨርስቲ (ፕሮፌሰር ኪሙራ፣ ፕሮፌሰር ሺጊታ፣ ዶ/ር ካኔኮ፣ ዶ/ር ሳሙራ፣ ዶ/ር ሚያዛኪ፣ ዶ/ር ዋካማትሱ፣ ዶ/ር ኢኬዳ፣ ሚስተር ማትሱኩማ – እንደ አመቻች ወይም አስተናባሪ ሲያገለግል የነበረ፣ ሚስተር ሃጊዋራ፣ ሚስተር አካጊ) ነበሩ
ከሚያዛኪ ዩኒቨርስቲ (ፕሮፌሰር ካሜ፣ ዶ/ር ፉኩባያሺ፣ ሚስተር ሳቶ) ነበሩ
ከኤሂሚ ዩኒቨርስቲ (ፕሮፌሰር የሹሃራ)
ከናጎያ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት (ዶ/ር ኢዋይ)
ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ (ዶ/ር ግርማ፣ ዶ/ር ሲሳይ፣ ዶ/ር ፍጹም)
ከጃፓን ኢምባሲ (ሚስተር ኤዳሙራ)
ከጃፓን የአለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ከአሁን በኋላ ጃይካ እየተባለ ከሚጠራው) ሚስተር ማትሱማያ፣ ሚስተር ሱዙኪ፣ ሚስ ናካጂማ፣ ሚስ አበባወርቅ ነበረ፡፡
የጂንካ ዩኒቨርስቲ አባላትና ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አባላት ለስብሰባው ተጋብዘው የነበሩ ቢሆንም በስብሰባው ላይ መገኘት ያልቻሉበት ምክንያት በቂ የኢንተርኔት ኮኔክሽን ባለመኖሩ መሆኑ አብራርተዋል፡፡

በፕሮፌሰር ኪሙራ እና ዶ/ር ሲሳይ ባደረጓቸው ንግግሮች ስብሰባው ተከፍቶ በየጊዜው/በመደበኛነት የኢንተርኔት መሳሪያዎቻው በመጠቀም በአሁኑ ወቅት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩም ቅሉ እያንዳንዳቸው ስለ ተግባሮቻቸው በፍጥነት ተግባቦትን ለመፍጠር እና ወደፊት ስራዎቻቸውን ለመፈጸም/ለማሳለጥ አቅደዋል፡፡

ሚስተር ማትሱማ በኢትዮጵያ እና ጃፓን ስላለው ወቅታዊ የኮቪድ-19 ሁኔታ በመጀመሪያው የስብሰባው ክፍለ ጊዜ ሪፖርት አድርገዋል፡፡ ቢያንስ በ2012 አመተ ምህረት ውስጥ በጃፓን እና በኢትዮጵያ መካከል ጉዞዎችን ማድረግ አዳጋች ሊሆን እንደሚችል አሳይቷል፡፡ ይህንን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በእያንዳንዱ ክፍል ስር የሚፈጸሙ ተግባራት ተረጋግጠው ተቀምጧል፡፡ በተጨማሪም “የመቆጣጠሪያ ወረቀት” ከስብሰባው በፊት ለእያንዳንዱ አባል አስቀድሞ እንዲደርሳቸው በመደረጉ የፕሮጀክቱ አባላት ይህንኑ አረጋግጠውታል፡፡

በሁለተኛው ክፍለ ጊዜ በብዙ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡- ስለወቅታዊው የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ሁኔታ፣ በጊዜ ሰሌዳ ስለተቀመጠው የተመረጡ ፋብሪካዎችን ለማግኘት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተሸከርካሪዎችን ሁኔታ መገንዘብ እና የስኮላርሽፕ ተማሪዎችን ቅበላ ደረጃ/ሁኔታ የመስክ ጉዞ ውይይት ተደርጎባቸው ነበር፡፡ ከዚያም ፕሮጀክቱ ወደፊት በሩቅ ጊዜ ውስጥ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን  አባላት ጋር ስብሰባ ስለሚደረግባቸው ሁኔታዎች ፕሮጀክቱ ለይቶ ያስቀመጠ ሲሆን የተሸከርካሪ ማኔጅመንትን ጉዳይ እልባት ሰጥቶታል፡፡

ከዚያም ስብሰባው በጃይካ እና በኢምባሲው በተሰጡ አስተያየቶች ፕሮጀክቱ እነዚህን አዳጋች ሁኔታዎች እንደሚቋቋማቸው እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በኮቪድ-19 ተጽእኖ ከባድ ጫና ስለደረሰበት ኢኮኖሚውን እንዲያገግም አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ያላቸውን ተስፋ በመግለጽ ስብሰባው ተጠናቋል፡፡