በመጋቢት 2023 ፕሮፌሰር ፉኩባያሺ ከሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ፣ ፕሮፌሰር ካኔኮ እና ፕሮፌሰር ሺጌታ ከኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ወደ ጂንካ ለMNGD ፕሮጀክት ስራ ተጉዘዋል።
የጉብኝቱ ዋና አላማ በጂንካ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ ለሚደረገው ለfull-scale driving experiment ሙከራ ዝግጅት ነበር። ፕሮፌሰሮቹ በዩንቨርስቲው ግቢ የአካባቢ ጥበቃ ስራን የሚሰሩ ሰራተኞችን በማግባበት ስራውን እንዲሰሩ እና ጥቁር መረሬ አፈር በለበት አካባቢ ደግሞ 20ሜ x 20 ሜትር የሆነ የሙከራ ቦታ እንዲያዘጋጁ አድርገዋል።
ምንም እንኳን በየቀኑ ዝናብ ይዘንብ የነበረ ቢሆንም የፀሃይ ብርሃን በታየ ቅጽበት ሁሉ አረም መንቀልና እና ቦታውን የማጽዳት ስር በእጅ ይከናወን ነበር፡፡ የተሽከርካሪ መቆያ ቦታዎች እና ለቁሳቁስ ማከማቻ የሚያገለግሉ ቦታዎችም በጠጠር እና በአሸዋ መሸፈን ስለነበረባቸው በአህያ ጋሪዎች የጠጠር አፈርን በማጓጓዝ ቦታዎቹ እንዲሸፈኑ ተደርጓል፡፡ ስለዚህ እንደ ቅድመ ሙከራ በአንድ አካባቢ (5 ሜ x 6 ሜትር) እርጥብ እና ጭቃማ ጥቁር አፈርን ከ”Celldoron” ጋር በመደባለቅ ፕላስቲክ በማድረግ በጠጠር አፈር ተሸፍኗል፡፡
የጠጠር መስፋፋት ሂደት አፈሩን ማድረቅን የሚጠይቅ በመሆኑ ተመራማሪው ሚስተር ማትሱኩማ እና ሌሎች ሰራተኞች የአየር ሁኔታ እንዳገገሙ ወደፊት የሚሰሩት ይሆናል፡፡