የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

“የመስክ ሪፖርት 022” በድህረ ገጽ ላይ ተለጥፏል

መስከረም 2021, አዲስ አበባ, ፎቶ በማስኩማ

★ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት እየመጣ ነው.... ! 

ኢትዮጵያዉያን የራሳቸዉን እና የጎርጎርያን የዘመን አቆጣጠር ይጠቀማሉ። ኢትዮጵያ የ2014 ዓ.ም አዲስ አመትን መስከረም 11 ቀን 2021 አ.አ በደስታ ትቀበላለች። 

ይህ ወቅት በጃፓን በጣም ሞቃታማ ወቅት ሲሆን በአዲስ አበባ ግን የዓመቱ ዝናባማ እና ቀዝቃዛ ወቅት ነው። መስከረም ሲጠባ ቅዝቃዛዉ እየቀነሰ ይሄዳል። መልክዓ ምድሩ በዚህ ወቅት ብቻ በሚያብብና የኢትዮጵያ አዲስ ዓመትን በሚያመላክት በአዴይ አበባ ተሸፍኗል። በዚህ ወቅት በሁሉም የገበያ ማዕከሎች እንዲሁም በሕንፃዎች ላይ ቢጫውን አበባ (አዴይ አበባ) በማስመሰል የተሠሩ በርካታ ጌጣጌጦች ይታያሉ። ፕሮጄክታችን በቀጠለ ቁጥር በዓመት ሁለት ጊዜ የዘመን መለወጫ ስሜትን ማጣጣም እንችላለን።

መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

እንቁጣጣሽ!!

*በዚህ ጉዳይ ላይ የተጻፈ ጽሁፍ እዚሁ ያገኙታል፡፡