የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

“የመስክ ሪፖርት 046″ በድህረ ገጽ ላይ ተለጥፏል

መስከረም 9፣ 2022 አዲስ አበባ (ፎቶ በሃጊዋራ)

መልካም አዲስ ዓመት!

የጊዜ ማሽን አላዘጋጀሁም… የምሬን ነው ። በጎርጎሮሳዊያን አቆጣጠር መስከረም 11 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ መስከረም 1 የ2015 አዲስ አመት የመጀመሪያ ቀን እንቁጣጣሽ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡      

አዲስ አበባ ከተማ የአዲስ አመት መባቻ ምልክት በሆነችው የአደይ አበባ ደምቃለች አሸብርቃለች። የአደይ አበባ ኃይል ከዚህ ቀደም ከአበባው ጋር ምንም ትውውቅ የሌለውን ልቤ እንኳን ለአዲሱ ዓመት የተለየ ስሜት እንዲሰማው አድርጎታል፡፡ በከተማው ከወትሮው በተለያ ሁኔታ በየቦታው ብዙ ዶሮዎችና ፍየሎች ይታየሉ።

በጃፓን አዲስ አመት በመጣ ቁጥር ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር በመሆን በጠረጴዛ ላይ ቀለም እንጨምር እንደነበረ  አስታውሳለሁ፡፡ ምንም እንኳን ይህንን የአዲስ ዓመት ዋዜማ ከቤተሰቤ ርቄ ባሳልፍም፣ የጃፓን አዲስ ዓመትን በዓመት ሁለት ጊዜ ማክበር እንደሚቻል ሳስብ ተፅናንቻለሁ፡፡ አዲሱ ዓመት መንፈሳችንን ያድሳል እንድሁም  አዲስ ጉልበት ይሰጠናል። ፕሮጀክታችንን ወደፊት ለማራመድ እንዲህ አይነት የመንፈስና የጉልበት መታደስን እንፈልጋለን።

*በዚህ ጉዳይ ላይ የተጻፈ ጽሁፍ እዚሁ ያገኙታል፡፡