ጥቅምት 26 ቀን 2022 በኢትዮጵያ ከሚገኘው ከጃፓን ኤምባሲ እና ከጃይካ ኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት የተውጣጡ ስድስት የስራ ኃላፊዎች በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ የሚገኘውን የMNGD ፕሮጀክት እንቅስቃሴን ለሁለት ቀናት ጎብኘተተዋል። ጉብኝቱ በጃፓን ኤምባሲ Grant Assistance for Grassroots Human Security Project የገንዘብ ድጋፍ የተገነባውን ሁለገብ የስልጠና እና የትምህርት ማዕከሉን ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ ርክክብ ከማድረግ ጋር ተያይዞ የተዘጋጀ ነበር። ይህንን ጉብኝት ለማድረግ አምባሳደር ኢቶ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበር ቢሆንም ከአቅም በላይ በሆኑ ሁኔታዎች ምክንያት በለመቻለቸው እሳቸውን በመወከል ሚስተር ታካሃሺ (የጃፓን ኤምባሲ ፀሃፊ ፣ የኢኮኖሚ ትብብር ዳይሬክተር) እና ሚስተር ዮሺዳ (የጃፓን ኤምባሲ ፀሃፊ) የተገኙ ሲሆን የGrassroots Project ፕሮጀክት ዳይሬክተር ወይዘሮ ታናካ እንዲሁም ከጃይካ ኢትዮጵያ ጽ/ቤት አቶ ሞሪሃራ (ዳይሬክተር)፣ አቶ አሚሚያ እና ወ/ሮ አበባወርቅ አበበ ተገኝተዋል።
የጉብኝት ቡድኑ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጂንካ ከደረሰ በኋላ በቀጥታ ያመረው ወደ ደቡብ ኦሞ የምርምር ማዕከል (SORC) እና በጂንካ ከተማ ኮረብታ ላይ ወደምገኘው ሙዚየም ነበር፡፡ ቡድኑ እዚያ እንደደረሰም የMNGD ፕሮጄክት አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ሺጌታ እና ዶ / ር ካኔኮ (ኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ) ከዶ / ር ኩሴ (የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት) እና ዶ / ር ኢሊያስ (የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት) ጋር በመሆን አቀባበል አድርገውላቸዋል.፡፡ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኩሴ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ ፕሮፌሰር ሽጌታ “Field Research Activities of Kyoto University in Ethiopia: In Relation to Social Contribution and Development Assistance in South Omo” በሚል ርዕስ በሙዚየም አዳራሽ ለተገኙት ገለጻ አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪም ፕሮፌሰር ሽጌታ በጃፓን ኤምባሲ በGrant Assistance for Grassroots Human Security ፕሮጀክት እና ከጃይካ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተከናወኑ የምርምር እና የትብብር ስራዎችን አስተዋውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር እየተካሄደ ያለውን የMNGD ፕሮጀክትን ሂደትም አብራርተዋል።
በመቀጠልም በደቡብ ኦሞ የሚኖሩ 16 ብሄር ብሄረሰቦች የዕለት ተዕለት መጠቀሚያ ቁሳቁሶችንችና ቅርሶችን እንዲሁም ባህለዊ ንብረቶችን የያዘውን ሙዚየሙን ጎብኝተዋል። ከዚያም በጃፓን ኤምባሲ Grant Assistance for Grassroots Human Security ፕሮጀክት በተሰጠው የገንዘብ ድጋፍ የ SORC አካል ሆኖ የተገነባውን ቤተመፃህፍት እና የምርምር ማዕከሉን ጎብኝተዋል።