የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

MNGD ዓለም አቀፍ የተማሪዎች አውደ ጥናት

አውደ ጥናቱሰኔ 29፣ 2022 በበየነ መረብ የተካሄደ ሲሆን፤ ይህ ወቅት ደግሞ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የአ.አ.ሳ.ቴ.ዩ የግንባታ ጥራትና ቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከል እና ሲቪልና የአርክቴክቸር ምህንድስና ኮሌጅ ወርሃዊ ሴሚናር የሚካሄድበት ግዜነበር። በአውደ ጥናቱ በሚያዛኪ ፣ በኤሂሜ እና በዮቶ ዩኒቨርሲቲዎች የሶስተኛ ዲግሪያቸውን እየተከታተሉ ያሉ ተማሪዎች የምርምር ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የጥናቱ አቅራቢዎች ፤-

ዕጩ ዶ/ር ፍሬሃይለአብ አድማሱ ጊዲቦ (በጃፓን ኤሂሜ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል እና አካባቢ ምህንድስና ትምህርት ክፍል፣ መምህር እና ተመራማሪ ሲሆኑ ፣  አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል  ባልደረባ ናቸው፡፡)
የጥናቱ ርዕስ “Simulation of Pseudo-expansive Black Cotton Soil by Using Combination of Bentonite and Kasaoka Clay Soils”

ዕጩ ዶ/ር አለምሸት በቀለ (ታደሰ በጃፓን ሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ፋኩልቲ ተማሪና በአአሳቴዩ በምህድስና አርክተክቸር ኮሌግጅ የሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል ባልደረባ ናቸው፡፡)
የጥናቱ ርዕስ “Effect of Diatomaceous Earth on Desiccation Cracking of Expansive Soils”

ዕጩ ዶ/ር ተሾመ ብርሃኑ (በጃፓን ኪዮቶ ዩኒቨርሲቲ የሲቪል እና ምድር ሃብት ምህንድስና ትምህርት ክፍል የዶክትሬት ተማሪና በአአሳቴዩ  ጉምቱ ተመራመሪ ናቸው፡፡)
የጥናቱ ርዕስ “Mechanical Properties of Soils Treated with Fine Shredded Paper (FSP) and Hydrated Lime”