የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የመንገድ ጥገና/ክብካቤ ሰርቶ ማሳያ

ፕሮጀክቱ በደቡብ ኦሞ ዞን የመንገድ ጥገና/ክብካቤ የሰርቶ ማሳያ ስራ በመንደር “B” ነዋሪዎች በሁለት ሳምንታት ከህዳር 15 ቀን 2012 ዓ.ም ተተግብሯል፡፡ በፕሮጀክቱ ውስጥ የተጠቃለሉት የሰርቶ ማሳያ ክፍል 3 ለመንገድ ጥገና/ክብካቤ እና ለዚህ ተግባር በመጀመሪያው ሙከራ የመንገድ ግንባታ/ኮንስትራክሽን ልኬት የኦፕሬሽን/የስራ እንቅስቃሴ ሞዴል አቋቁሟል፡፡ የዚህ የሙከራ ተግባር አላማ የአካባቢውን ሁኔታ ለመገንዘብ በተለይም በመንገድ ላይ የሚደርሱ የአደጋ ጉዳቶችን በተመለከተ ከአስተዳዳሪዎች፣ ዩኒቨርስቲዎች እና ሌሎች ህብረየህብረተሰብ አካላት ጋር በመተባበር ስራውን የአካባቢው ኑዋሪዎች በተደራጀ መልኩ ከእነዚህ አካላት ጋር ተባብረው እንዲሰሩ ለማድረግ ነው፡፡ የሰርቶ ማሳያ ጣቢያው የሚገኝበት አድራሻ በኤሪያል ፎቶግራፎች ከሚገኙ መረጃዎች፣ ከአካባቢው ኑዋሪዎች ጋር በሚደረግ ቃለ መጠየቅ እና ከአካባቢው ከንቲባ ጋር በመመካከር እና ዶ/ር ገብሬ የጂንካ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ለምሳሌ ጥቅምት 7 ቀን 2002 ዓ.ም የሰርቶ ማሳያ ስራው ከመጀመሩ በፊት ከአካባቢ ኑዋሪዎች ጋር በተደረገው ስብሰባ መረጃ እንዲደራጅ ተደርጎ የነበረው በዶ/ር ካኔኮ የኪዮቶ ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና በሌሎች በተደራጀው መረጃ ላይ በመመስረት የሰርቶ ማሳያ ጣቢያውን መወሰን ተችሎአል ፡፡ በመንደሩ ስብሰባ ላይ ወደ 100 ኑዋሪዎች ተሳትፊ ሆኖዋል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ ይህ ፕሮጀክት ለመንገድ እድሳት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ተብራርቷል፡፡ በስብሰባው ላይ የመንገድ እድሳት ስራን በሰርቶ ማሳያ ጣቢያው በተግባር እንዲፈጸም ተወስኖ የነበረው ለአካባቢው ኑዋሪዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲያውቁ ለማድረግ ነበር፡፡ ይህንን ስራ በጋራ በሚሰሩባቸው የስራ ቀናት ለመስራት ተስማምቷል፡፡

[የመንገድ ግንባታ/ኮንስትራክሽን ዝግጅት]

1)መንገዶች ያሉባቸውን ችግሮች መገንዘብ

ዶ/ር ፉኩባያሺ (በሚያዛኪ ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር) እና ሚስተር ሳቶ የተባሉት አንድ የድህረ ምረቃ ተማሪ በመንገድ ሁኔታዎች ላይ የዳሰሳ ጥናት ዝግጅት ስራን ሰርቷል፡፡ የሰርቶ ማሳያ ጣቢያው በመንደር “B” ውስጥ ከሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በ125 ሜትር ላይ የሚገኝ መንደር ነው፡፡ ጥልቀት ያላቸው በተዳፋት መሬት ላይ በሚወርድ ጎርፍ ጥልቀት ያላቸው ጉድጓዶች በመንገዱ እና በትምህርት ቤቱ ዙሪያ የውሃ መፍሰሻ ቦይ ባለመኖሩ ምክንያት ጥልቀት ያላቸው ጉድጓዶች በጎርፍ ሊፈጠሩበት ችለዋል፡፡

2)የሳይት የዳሰሳ ጥናት

ለመንደሩ የጎበዝ አለቃ/ሃላፊ እና ሌሎቹም አጠቃላይ የተግባራት ገለጻ ከተደረገላቸው በኋላ ቁመታዊ ተዳፋት እና የመስቀለኛ ክፍል ቅርጽ ባለው መንገድ ላይ የተሰራው የሰርቶ ማሳያ ጣቢያ የዳሰሳ ጥናት ተደርጓል፡፡

3)ፕላን መሳል እና ማቴሪያሎችን መሰብሰብ

በዳሰሳ ጥናቱ መሰረት ፕላን በመሳል ለግንባታው/ኮንስትራክሽኑ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን ብዛት/መጠን በማስላት እንደ አፈር የመሳሰሉትን በመቁረጥ እና ለሙሌት፣ ጠጠሮችንና ሌሎች የግንባታ ማቴሪያሎችን መጠን አስልቷል፡፡ በጣቢያው አቅራቢያ ከሚገኘው ኳሪ ለእግረኛ መንገድ የሚሆን ጠጠር መርጠዋል፡፡

4)የአካባቢውን ህብረተሰብ ተግባራት ስራ ምልከታ

በመንደር “B” የሰርቶ ማሳያ ስራው ከመጀመሩ በፊት የህብረተሰቡን ስራ ምልከታ አድርጎ ነበር፡፡ በዋናው መንገድ ላይ የሚገኙ አሸንዳዎችን መልሶ ለማቋቋም ህብረተሰቡ ሙከራ ተደርጎ ነበር፡፡ የሰርቶ ማሳያ ተግባሩ የተፈጸመው ለሁለት ሰአታት ከጠዋቱ 1፡00 ሰአት ጀምሮ ህብረተሰቡ ስራ ባልነበረው ቀን ነበር፡፡ በእሁድ እና ቅዳሜ ቀናት የገበያ ቀናት ስለሆኑ የፕሮጀክቱ ስራዎች አልተሰሩም፡፡

[ኮንስትራክሽን/ግንባታ]

1)የአሸንዳዎች ቁፋሮ

ከመንደሩ የተሰባሰቡ ከ150 ሰዎች በላይ  በጋራ ሆነው ሰርተዋል፡፡

2)የመንገዱን አካል የመደልደል ስራ

አሸንዳዎቹን በመቆፈር አፈሩን ያሸጉት በአፈር/ድንጋይ በተሞሉ ማዳበርያዎች ሲሆን እነዚህንም ከረጢቶች ጥልቀት ባለው በጎርፍ በተፈጠረው ጉድጓድ ውስጥ አስቀምጠውታል፡፡

3)አሸንዳዎቹን ቅርጽ ማስያዝ

4)ጠጠሮቹን መደልደል

በከባድ ተሸከርካሪዎች ጠጠሮችን ያመጡ ሲሆን ለመንገድ አካል የድልዳሎ ስራ እንዲቀመጥ/እንዲበተን አድርጎታል