የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የምርምር ስብሰባ በኤሂሜ ዩኒቨርሲቲ

በየካቲት 3 እና 4 በኤሂም ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ቀናት የተካሄደው የምርምር ስብሰባ የMNGD ፕሮጀክት ዋና መስራችና የቡድኑን መሪ ፕሮፌሰር ኪሙራ እና የፕሮጀክቱን ዋና ተመራማሪዎን ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ያገናኘ ነበረ፡፡

በዝህ ስብሰባ የእያንደንዱ ክፍል እድገት የተገመገመ ሲሆን የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችምን በጋራ ለይተዋል፡፡  የሰውነት ቋንቋ እና የእጅ ምልክቶችን በመጠቀም ሞቅ ያለ ውይይት የተደረገበት በጣም ውጤታማ ስብሰባ ነበር ።

በተጨማሪም ከስብሰባው በፊት በተካሄደው የኢሂሜ ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ፋኩልቲ የላብራቶሪ ጉብኝት ወቅት የክፍል ሁለት መሪ የሆኑት የፕሮፌሰር ያሱሃራ ተማሪዎች ፖስተሮችን በማቅረብ  ስለ ቤተ-ሙከራው እንቅስቃሴና መሳሪያዎች በዝርዝር አስረድተዋል። በMNGD አለም አቀፍ ፕሮግራም የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪ የሆኑት ሚስተር ፍሬሃይለአብም የምርምር ፕሮጀክታቸውን ገለፀ አቅርበዋል፡፡