የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት ክፍል 3
ወደ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ያቀናነው የናሙና ቅንብር ትንታኔ የሚሰራልን የኤሌክትሮን ማይክሮስኮፕ (SEM) ለመጠየቅ ነበር፡፡ ወደ ቤተ-ሙከራው ስናቀና ቀጠን ረዘም ያለና በነጭጋዋኑ ተውቦ የተመልካችን ቀልብ ከሩቅ የሚስበው የላብራቶሪው ረዳት፣ በቅልጥፍና በጣም ጥሩ በሆነ ሁኔታ የSEM ናሙናዎችን አዘጋጀልን። የላብራቶሪው ረዳቱ ቁመናው ብቻ አልነበረም የሚያማርከው ፤ሳይንስ የሰዎችን ሁለንተናዊ ስብዕናን በዲሲፕሊን እየቃኛ “ሳይንቲስቶች” ያደርጋቸዋል እንደሚባለው ሁሉ፤ እርሱም በእረግጥም ሳይንቲስት ነበር፡፡