ከ2020 ጀምሮ የMNGD ፕሮጀክት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ የተነሳ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የአየር ሁኔታ ትንበያ / የሜትሮሎጂ/ መሳሪያዎች ተተክለው አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው። በዝህ የአየር ሁኔታ ትንቢያ / የሜትሮሎጂ/ መሳሪያ አማካይነት የአዲስ አበባን (የሙቀት መጠን፣የዝናብ ሁኔታን፣የፀሃይ ፣የንፋስ ፍጥነት ወዘተ) ማወቅ እንችላለን። →★
Monthly Archives: July 2022
3 posts
4ኛው የጋራ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ መስከረም 1/2022 ቀን (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከ9፡30 – 15፡30 /በጃፓን ሰዓት አቆጣጠር ከ15፡30 – 21፡30) ተካሂዷል፡፡ የስብሰባው የተካሄደው አዲስ አበባ በሚገኘዉ ሳፋየር ሆቴል እና በበየነመረብ ነበር፡፡
MNGD የአ.አ.ሳ.ቴ.ዩ. አለም አቀፍ የተማሪዎች አውደ ጥናት እ.ኤ.አ ሰኔ 28/2022 በበየነ መረብ ተካሄዷል፡ በዕለቱ በሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ፣ በኤሂሜ ዩኒቨርሲቲ እና በዮቶ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ/ የዶክትሬት/ ዲግሪያቸውን የሚማሩ ተማሪዎች የምርምር ውጤታቸውን አቅርበዋል። ተማሪዎቹ ጥናታቸውን ካቀረቡ በኋላ በአ.አ.ሰ.ቴ.ዩ ቀይ ምንጣፍ አዳራሽ ከተሰበሰቡ ታዳሚዎች እና በበየነመረብ ስከታተሉ ከነበሩ ታዳሚዎች ጋር ውይይት ተደረጓል።