የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

መልዕክት

 

በኢትዮጵያ በርካታ የገጠር ማህብርሰብ በአግባቡ ባልተጠበቁና ባልተጠገኑ መንገዶች ምክንያት ተደራሽ ሳይሆኑ ቆይተዋል። የዚህ ፕሮጀክት አላማ አገር በቀል ከሆኑ አፅዋት በሚጎለብት የአፈር ማረጋጊያ ግብአት የመስፋፋት ባህሪ ያለው የጥቁር አፈር (መረሬ) አፈርን ተረጋግቶ በቦታው እንዲቆይ ለማድረግ የገጠር መንገዶችን ስራና ማሻሻያ ሙከራ ችግሩ ባለባቸው ቦታዎች ለመተግበር ነው ። ፕሮጅክቱ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት ወጣት ኢትዮጵያውያንና ጃፓናውያን ተመራማሪዎችን የሚያሳትፍ ይሆናል ።

ፕሮፈሶር ማኮቶ ኪሙራ ፣ ክዮቶ ዩኒቨርስትይ

 

 

ይህ የ “መንገድ” ምርምር ፕሮጀክት የመስፋፋት ችግር ያለበት የጥቁር አፈር (መረሬ) ምርምር ፕሮጀችት ነው ። ፕሮጀችቱ ለ 5 ዓመት የሚቆይ ሲሆን ፣ በዚህ 5 ዓመት ግባችን የአፈር ማረጋጊያ ሞዴል ለማጎልበትና የመተግበርያ መመርያዎችን ለመንደፍ ፣ አንዲሁም የ ምርምሩን ዉጤት/ግኝቶችን ለተጠካምሚዎች በህትመት መልክ ለማሰራጨት ነው።

ዶ /ር መሳይ ዳንኤል ቱሉ ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲትይ