በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከሚደረገው የሙሉ የአሽከርካሪነት ሙከራ የቅድመ ዝግጅት ስራ ጎንለጎን መንገድ እንድሻሻል የአካባቢው ነዋሪዎች በጠየቁት መሰረት ዶ/ር ፉኩባያሺ ከሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ፣ ዶ/ር ካኔኮ እና ዶ/ር ሺጌታ ከኪዮቶ የ2.7 ኪሎ ሜትር መንገድ ላይ የዳሰሰ ጥናት አካሂደዋል። የመንገድ ማሻሻያ ግንባታ ዳሰሰው ጥናቱ አስፈላጊውን ድልድዮችን እና ፍሳሽ ማስወገጃን ያከተተና ከአካባቢው ቀያሾች እና ዲዛይነሮች ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን ይህንን የማሻሻያ ፕሮጀክት ኃላፊነት ከሚወስደው ከወረዳ አካባቢ አስተዳደር ጋር ተወያይተዋል።
የሚገነባው መንገድ መንደሩንና ጤና ጣቢያውን የሚያገናኝ አቋራጭ መንገድ በመሆኑ ለአካባቢው ነዋሪዎች እጅግ ጠቃምና ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ይጠበቃል። በእቅዱ መሰረትም የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመንገድ ግንባታው በፊት ያለውን ነባራዊ ሁኔታ አስመልክቶ በአካባቢው በሚደረገው የዳሰሰ ጥናት ላይ እንዲሳተፉ ተጠይቀዋል።