ይህ የመጀመሪያ ወደ ውጭ አገር ጉዞዬ በመሆኑ ብዙ ነገር ያስደንቀኝ ነበር፡፡ በጃፓንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ልዩነት ያለማቋረጥ ይገርመኝ ነበር። በመንገድ ላይ ስጓዝ የማገኛቸውን ሰዎች ብዙ ጊዜ “ጤና ይስጥልኝ! ሰላም! ሰላም ነው? ማለት የአገሩ ባህል ስለሆነ ግድ ነበር፡፡ መኪና ማሽከርከሩ ደግሞ ከጃፓን በተለየ መንገድ በግራ በኩል ነው፤በጃፓን ወደ ቀኝ መታጠፍ አልወድም ነበር፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ወደ ግራ መታጠፍ አልወድም።