የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

“የመስክ ሪፖርት 039″ በድህረ ገጽ ላይ ተለጥፏል

ግንቦት 24፣ 2022፣ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ፎቶ በሃጊዋራ)

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት ክፍል 1

ከተመራማሪ ማትሱኩማ እና አቶ  ወንዲሙ ጋር በመሆን የሙከራ ጥንቅር ለመቀላቀል እና ትንታኔለመስጠት የሚረዳንን የኤክስሬይ ዲፍራክሽን (XRD) እና ስካኒንግ ኤሌክትሮን ማይክሮስኮፕ (SEM) ለመጠየቅ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን ጎብኝተን ነበር። የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችውና ከአዲስ አበባ ባስተ ደቡብ ምስራቅ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በአዳማ ከተማ ውስጥ የሚገኝ አስደናቂ ተቋም ነው፡፡ ከሩቅ በግርማ ሞገሱ የተቀበለን የዩኒቨርሲቲውን መግቢያ በር  ተከትለን ወደ ውስጥ ስንገባ ፤ግቢው በአረንጓዴ እፀዋት  የተሞላ ከመሆኑ የተነሳ መድረሻችንን ለማግኘት እንኳን ከብዶን ነበረ። በግቢው ውስጥ ሚሰማውን  ያማረውን የወፎች ዝማሬን ልናሰማችሁ አለመቻላችን ያሳዝናል።

*በዚህ ጉዳይ ላይ የተጻፈ ጽሁፍ እዚሁ ያገኙታል፡፡