የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

“የመስክ ሪፖርት 052″ በድህረ ገጽ ላይ ተለጥፏል

መስከረም 22፣ 2022፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ፎቶ በአሳይ)
ጥቅምት 4፣ 2022፣ አ.አ.ሳ.ቴ.ዩ (ፎቶ በኪዶ)
ጥቅምት 4፣ 2022፣ አ.አ.ሳ.ቴ.ዩ (ፎቶ በኪዶ)

ኢትዮጵያ ውስጥ ማየትና መንካት በጣም የጓጓሁት ነገር ቢኖር ውሃ ስይዝ/በእርጥበት ጊዜ/ የሚያብጠውን በደረቅ ወቅት ደግሞ የሚሰነጠጠቀውን ጥቁር መረሬ አፈርን  ነበር፡፡ ይህ በመላው ኢትዮጵያ የተሰራጨው ጥቁር መረሬ አፈር ሲደርቅ ሸክላ /አፈር ብቻ ነው/, ነገር ግን ትንሽ ውሃ ሲያገኝ ደግሞ ተለጣጭና ተጣባቂ  /የመለጠጥና የመጣበቂ/ በህርይ አለው የአፈር አይነት ነው፡፡ አፈሩ በጣም ብዙ ንጥረ-ነገር የያዘና በደንብ ሰብል የሚያበቅል እና ምርት በደንብ የምሰጥ ይመስላል ፡፡ ነገር ግን ይህን አፈር በመንገድ ላይ ቢናደርግ/ቢናነጥፍ/ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስብ ነበር፡፡

ይህንን አፈር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሁሉም ቦታ አገኘሁት።  በዩንቨርስቲው ውስጥ ያሉት  የእግረኛ መንገዶች በኮብልስቶን የተሸፈኑ ቢሆንም ከድንጋዩ ስር ያለው መሬት ለስላሳ በመሆኑ የጎማ ዱካዎች በግልፅ ይታያሉ። ከኮብልስቶን ስር ያለው ጥቁር መረሬ አፈር  በመሆኑ እርጥበት/ውሃ/ ሲያገኝ የመለጠጥ ችግር ያለበት አፈር ነው። ወደ አ.አ.ሳ.ቴ.ዩ በደረሰበትን የመጀመሪያ ቀን ወደ 5 ሴ.ሜ ጥልቀት የነበረ ቦይ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ከ10-15 ሴ.ሜ የሚደርስ ጥልቅ የጉድጓዱ ሲሆን ከጥቂት ቀናት ዝናብ በኋላ ከባድ ማሽነሪዎች  መንገድ ያለፉ ይመስል ጎርጉዶ ነበር ። በፕሮጀክክቱ  እየተሞከረ ያለውን ከዕፅዋት የተቀመሙ ማሻሻያዎችን በዚህ አፈር ላይ ብንጨምር ምን ሊፈጠር እንደሚችል አሰብኩ።

በሙከራዎቻችን ወቅት ከዕፅዋት ከተቀመሙ ማሻሻያዎች ጋር የተደባለቁ የአፈር ናሙናዎችን በጊዚያዊነት ከላቦራቶሪ ውጭ ባለው መሬት ላይ እናስቀምጥ ነበር። በዚሁ የቤተ-ሙከራ አከባቢ የአፈር ናሙናን ለመውሰድ የሆነ ቦታ ስረግጥ ከሌላው በታ በተለየ ለእግሬ ጥንካሬ ሲሰማኝ፤ ቦታው ከሌሎቹ  አከባቢዎች  ለምን ልዩ እንደሆነ ግራ ገብቶኝ ሚስተር ማትሱኩማ ብጠይቅ በሙከራው ስራ ጥቅም ላይ የዋለውንና ከእጸዋት ከተቀመሙ ማሻሻዎች  ጋር የተደባለቀ የናሙና ስራን ሚስተር ሺንጆ ከሶስት አመታት በፊት ያስቀመጠበት ቦታ እንደሆነ ነገረኝ። በዝህን ጊዜ ነበር ከዕፅዋት የተቀመሙ ማሻሻያዎች ውጤት እንደሚያመጡ የተሰማኝ ።

*በዚህ ጉዳይ ላይ የተጻፈ ጽሁፍ እዚሁ ያገኙታል፡፡