በአ.አ.ሳ.ቴ.ዩ ቤተ ሙከራ ውስጥ የተደረገ የጦፈ ውይይት
የቡድን 1 መሪ የሆኑት የሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ የስራ ባልደረባ ዶ/ር ፉኩባያሺ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አ.አ.ሳ.ቴ.ዩ) ቤተ ሙከራን ጎብኝተዋል። “ብረቱን በሞቀ ጊዜ ይምቱት” እንደሚበለው . በቅርቡ በተካሄደው የአጠቃለይ /GCC/ ስብሰባ ወቅት የነበረው የውይይት ግለት ሳይበርድ ቁልፍ አባላት በተገኙበት በቤተ ሙከራ ውስጥ ሞቅ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡በኮንፈረንስ ክፍል ውስጥ ባለው ጠረጴዛ ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶች ጥሩ ቢሆኑም የአንድ ሳይንቲስት እውነተኛ ግዛት በሆነው ቤተ ሙከራ ውስጥ የሚደረጉ ውይይቶች ያክል ኃይል የላቸውም ።