የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ትብብር ለዘላቂ ልማት
“የመንገድ አደጋን ለመቀነስ ለመንገድ ግንባታ አስቸጋሪ የሆነ አፈርን ከዕጽዋት ከሚወሰዱ ንጥረ ነገሮች የማሻሻል ስራ እና የልማት ሞዴል”

ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ጃፓን ደርሰዋል

“SATREPS MNGD ፕሮጀክት”   ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያ ሲቀበል ቆይቷል።

በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ  “SATREPS MNGD ፕሮጀክት”    እንቅስቃሴ ላይ አስተዋፅኦ ሲያደርጉ የቆዩ ሁለት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አስተማሪዎች ወደ ጃፓን መጡ። በጥቅምት ወር አቶ አለምሸት በቀለ ወደ ሚያዛኪ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ፋኩልቲ ተዛወሩ። እንዲሁም አቶ ፍሬሃይለአብ አድማሱ ወደ ኢሂም ዩኒቨርሲቲ ሲቪል እና ዬአካባቢ  ምህንድስና ዲፓርትመንት ተዛውረዋል። ምንም እንኳን በ ኮቪድ 19 ስርጭት ምክንያት ወደ ጃፓን መምጣታቸው ቢዘገይም፣ ሁለቱም ኅዳር 5፣ 2020  ጃፓን ደረሱ። በቶኪዮ በሚገኘው የውሸባ ማዕከል ውስጥ ከሁለት ሳምንት ጥበቃ ጊዜ በኋላ ወደ እያንዳንዱ አስተናጋጅ ዩኒቨርሲቲ ሄደዋል። በአሁኑ ወቅት አቶ አለምሸት ከሚያዛኪ ዩኒቨርስቲው ከፕሮፌሰር ፉኩባያሺ ጋር በመሆን ችግር ያለበትን አፈር ግዑዝ ባህሪ ለመረዳት ሙከራዎችን እያካሄዱ ሲሆን፥ ፍሪሃይላብ ከኢሄሜ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ያሱሃራ ጋር በመሆን ጥሩ ዱቄት ያላቸውን ተክሎች ውሃ የመሳብ ተግባር ላይ ሙከራዎችን በማድረግ ላይ ናቸው።